እንኳን ደስ አላችሁ!!
ጣና ክፍለ ከተማ ወደ አንደኛ ሊግ መግባቱን አረጋግጧል!!
ባሕር ዳር(ሐምሌ15/2016 ዓ/ም)፣ የአማራ ክልልን ወካዩ የጣና ክፍለ ከተማ በክልል ክለቦች ሻምፒዮናው ሶስተኛ በመውጣት ወደ አንደኛ ሊግ መግባቱን አረጋግጧል፡፡
ባሕር ዳር ከተማ ስፖርት ክለብ በሁሉም የከተማችን ክፍለ ከተሞች በሚያደርገው የታዳጊዎች ውድድር ከፍተኛ ነጥብ እያስመዘገበ ለመሆኑ ጣና ክፍለ ከተማ ምስክር ሆኗል፡፡
በተጨማሪም በ2016 በጀት ዓሜ የባሕር ዳር ከተማ የወንዶች እግር ኳስ ክለብ (ባሕር ዳር ከነማ) ደረጃውን አስጠብቆ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታውን አጠናቆ የአመቱን ጨዋታ ጨርሷል፡፡
የባሕር ዳር ከነማ ስፖርት ክለብ ከሚሰራቸው ስራዎች ውስጥ በዚህ ዓመት በርካታ ስኬቶችን የተጎናጸፈ ሲሆን የሴቶች ክለብ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከ2017 ዓ/ም ጀምሮ የሚጫወት መሆኑን ያረጋገጠ ሲሆን ጣና ክፍለ ከተማም ወደ አንደኛ ሊግ ማለፉ ለከተማችን እግር ኳስ ከፍተኛ ተስፋን የሰነቀ ነው፡፡
በድጋሜ እንኳን ደስ አለን!!
ድል ለባሕር ዳር ከተማ

Similar Posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *