ስለ ጨዋታው ያደረገው ቆይታ ከ ሶከር ኢትዮጵያ ጋር …
”ጨዋታው በጣም ጠንካራ ነበር። ሀዲያ ጠንካራ ስብስብ ነው ያለው የነበረው ቡድኑ ሳይበተን ያሉትን ይዞ ባሉት ላይ ደግሞ የተሻለ ክለቡን ሚያጠናክሩ ተጫዋቾችን ቀላቅሎ ነው የመጣው እና በሜዳ ላይ ፈታኝ ነበር። አግሬሲቭ ይጫወታሉ ጫና ፈጥረው ለመጫወት ይሞክራሉ ፈጣን የመስመር አጥቂዎች አሏቸው ጉልበተኞች ናቸው አንድ ለአንድ ግንኙነት ላይም እንግዲህ ተጫዋቾቻችን ይሄንን ጫና ተቋቁመው እንደምታስታወሱት ከመሸነፍ ነው የመጣነው ያንን ወደ ማሸነፍ ለመመለስ የነበረን ጥረት እጅግ በጣም የሚያስደስት ነው ይሄ ደግሞ የክለባችን መለያ ነው ከአንድ ሽንፈት ቶሎ ወደ ማገገም የምንመጣበት መንገድ በጣም ደስ የሚል ነው እና ምናልባት ወደ እራሴ ካላደላሁ በአሳማኝ ሁኔታ ጨዋታውን አሸንፈናል ብዬ አስባለሁ”
በሁለተኛው አጋማሽ መጀመሪያ ላይ መዘናጋቶች ነበሩ እና ምክንያቱ ምን ነበር?
”አዎ ይጠበቃል ባዶ ለባዶ ነው የወጣነው ልክ ስትገባ የመጀመሪያ ደቂቃዎች ላይ ጫናዎች ይኖራሉ ሚጠበቅ ነው። ተጫዋቾቻችን ጨዋታውን ተቆጣጠረውታል። የተሻለ የግብ ዕድል ፈጥረናል መጠቀም አልቻልንም በዛ ስሜት ውስጥ ሆነው ነው የገቡት ነገር ግን የራሳችንን የጨዋታ መንገድ ተከትለን እስከመጨረሻው ድረስ ከሄድን ጎል እንደምናገኝ እናውቅ ነበር እና ከተጫዋቾችም ጋር ያደረግነው የእረፍት ሰዓት ውይይትም ያው ነው ስለዚህ ልክ እንደገባን እንዳልከው ትንሽ መዘናጋቶች ነበሩ በራሳችን ኳሶች የተፈጠሩ ሆኖም ግን ቶሎ ወደ ሪትሙ ለመመለስ ችለናል እና የተሻለ እንቅስቃሴ አድርገናል።”
ከዚህ በፊት የቡድን ግንባታህ የመስመር አጥቂዎች ላይ ነበር አሁን አሁን ግን በተለይም ዛሬ በብዛት በመሃል ለመሃል የመሄድ ነገሮች አሉ እና ይሄን የጨዋታ መንገድ ትቀጥላላችሁ?
“እንመጣበታለን። ሁሌም ሞር እኩል አድርገን መጫወት ነው የመጀመሪያ ምርጫችን እንግዲህ የተለያዩ ተጫዋቾችን ለማየት ሞክረናል። በምንከተለው የጨዋታው መንገድ የዛሬ ጨዋታ ደግሞ ከክለቡ ከተጋጣሚያችን ከሚከተለው ጨዋታ ጋር ተያይዞ የመሃል ሜዳ ብልጫውን ለመቆጣጠር ለመውሰድ ይሄኛውን የጨዋታ መንገድ ተጠቅመን ነው የገባነው። ለዚህኛው ጨዋታ መንገድ የሚሆኑ ተጫዋቾችን በሜዳው ላይ ለመጠቀም ሞክረናል። እንደአጠቃላይ ግን በመስመር የመጫወት እንቅስቃሴው ለቲማችን ትልቁ የማጥቂያ መንገድ ነው እና የበለጠ አጠናክረነው የምንቀጥል ነው የሚሆነው።”
ምን ጊዜም የጣናው ሞገድ
ድል ለጣናው ሞገድ፤ ባሕር ዳር ከተማ!!