የጣናው ሞገድ ባሕር ዳር ከተማ የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሐሙስ ሰኔ  27/2016 ሰላሳኛ ሳምንት ሃዋሳ ዩንቨርሲቲ ስታዲየም የአመቱን የመጨረሻውን ጨዋታ አካሂዶ ነበር። በአመቱ የተካሄዱ የ30ሳምንታት ጨዋታዎች በድል የኳስ ሜዳ የተለየ ዘዬውን እየተጠቀመ የሜዳ ውስጥ ጥበብን ሲያስኮመኩመን ከርሟል። ብዙዎችም አድናቆትን ችረውታል። ድንቅ የአጨዋወት ጥበብን የተካኑ የዘምባባው ስር የሞገዱ ልጆች ከበርካታ ቡድኖች ላይ ነጥብ ነጥቀዋል፣ ነጥብ ተጋርተዋል፣ ነጥብ አጋርተዋል። ለዋንጫ የሚጠበቅ አቅምና የደጋፊዎችን ይሁንታ ያገኘው ባሕርዳር ከተማ ሳይታሰብ የአገርም የክለቡንም ቀኝ እጅ ባለ 23 ቁጥሩን አለልኝ አዘነን በድንገተኛ ሞት ተነጠቀ።
ሐዘን ሳይበግረው በሐዘን ውስጥ ሆኖ በድሬደዋ ሜዳ የሟች ጓደኛቸውን ምስልና ቲሸርት አንግበው ወደጨዋታ ተመለሱ። እስከ መጨረሻው ጨዋታ ድረስ ነጥብ መጣል በባሕርዳር ከተማ የማይታሰብ ነበር። ወይ ነጥብ ይወስዳሉ ካልሆነ ነጥብ ይጋራሉ እንጅ ሽንፈት የማይታሰብ ነበር። ከሀዘን መልስ የተገኘውን ድል የሟች ጓደኛቸው መታሰቢያ አደረጉ።

በ23 ቁጥር ቲሸርት ላይም የክለቡ ቦርድ በክብር እንዲቀመጥ ወሰነ። በየጨዋታው መክፈቻ ላይ ያ የሜዳ ውስጥ ተርቡ ባለጥበብ ሰው፣ የነገ ተስፋ ያልነው አለልኝ እየታሰበ የአመቱ የሜዳ ውስጥ አለም ተፈጸመ። ይህም እየሆነ ታዲያ የአመቱ ፕሪምየር ሊግ ሲጠናቀቅ ባሕርዳር ከተማ ከ16 ተፋላሚ ክለቦች ውስጥ 4ኛ በመሆን አጠናቋል።

ምስሎችን እነሆ✒️
ድል ለጣናው ሞገድ ባሕር ዳር ከተማ
The Office of PR & Communications, Bahir Dar City Sport Club

#follow Us on Social Media:
Website: www.bdsportclub.et
Telegram: https://t.me/BDSport_Club
Facebook; https://www.facebook.com/profile.php?id=100087337060004
Twitter; https://x.com/bdsportclub
Instagram; https://www.instagram.com/bd_sportclub
LinkedIn; https://www.linkedin.com/company/bdsport-club/
WhatsApp; https://whatsapp.com/channel/0029VacQrCH3WHTV9PbU072q
Victory for Wave of Lake Tana!
Office of PR & Communications, Bahir Dar City Sport Club

Similar Posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *