የጣናው ሞገድ ባሕር ዳር ከተማ የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የጣናው ሞገድ ባሕር ዳር ከተማ የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሐሙስ ሰኔ  27/2016 ሰላሳኛ ሳምንት ሃዋሳ ዩንቨርሲቲ ስታዲየም የአመቱን የመጨረሻውን ጨዋታ አካሂዶ ነበር። በአመቱ የተካሄዱ የ30ሳምንታት ጨዋታዎች በድል የኳስ ሜዳ የተለየ ዘዬውን እየተጠቀመ የሜዳ ውስጥ ጥበብን ሲያስኮመኩመን ከርሟል። ብዙዎችም አድናቆትን ችረውታል። ድንቅ የአጨዋወት ጥበብን የተካኑ የዘምባባው ስር የሞገዱ ልጆች ከበርካታ ቡድኖች ላይ ነጥብ ነጥቀዋል፣ ነጥብ ተጋርተዋል፣…