የባሕርዳር ከነማ ሶስት ተጫዋቾች በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር በኮከብ እጩ ነት ቀረቡ።

ሰኔ 26/2015ዓ/ም (ባሕርዳር ከነማ ስፖርት ከለብ፣ ባሕር ዳር) የ2015 ዓ.ም የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ተጨዋች ለመምረጥ በተደረገው እጩ ምልመላ ላይ ባሕርዳር ከነማ ሶስት እጩዎችን ማስመዝገብ ችሏል። በዚህ መሰረትም በእጩነት ከቀረቡ 7 እጩ ኮከብ ተጨዋቾች ውስጥ 3ቱ ከባሕርዳር ከነማ መመልመላቸው ይፋ ሆኗል። በመሆኑም ፉዓድዳር ፈረጃ ፣ያሬድ ባየህና አለልኝ አዘነ ከባሕር ዳር ከተማ በእጩነት ቀርበዋል። ሌሎች እጩዎች ቢንያም በላይ እና እስማኤል ኦሮ አጎሮ ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ባሲሩ ኡመር ከኢትዮጵያ መድኀን እንዲሁም ጌታነህ ከበደ ከወልቂጤ ከተማ በእጩነት ቀርበዋል፡፡ በምርጥ ግብ ጠባቂ እጩ ዝርዝር ደግሞ አቡበከር ኑራ ከኢትዮጵያ መድን፣ ፔፔ ሳይዶ ከሀድያ ሆሳዕና እንዲሁም ቢኒያም ገነቱ ከወላይታ ድቻ በእጩነት መቅረባቸውን የሊግ ኩባንያው መረጃ ያመላክታል፡፡ ስለሆነም የስፖርት ቤተሰቡ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ምርጫን እስከ ሰኔ 29 ቀን 2015 ዓ.ም እንዲያከናውን ጥሪ ቀርቧል፡፡ ድልና ስኬት ለጣናው ሞገድ ባሕር ዳር ከነማ

Similar Posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *